የሥነ አዕምሮ ምክር የምንሰጠዉ በ Evangelischen Zentrum Höchst ሲሆን በሚከተሉት ት/ቤቶችም የምክር ክፍል ዉስጥ አገልግሎት እንሰጣለን። እነሱም በ Adolf-Reichwein-Grundschule እና በ Käthe-Kollwitz-Grundschule in Zeilsheim. በየቦታዉ ያሉትን የምክር ሰዓታት ይመልከቱ።
Eይህ የምክር አገልግሎት ለወላጆች ና ለቤቴሰቦች ከት/ቤት አስተማሪ ሲሊካቸዉ፣ ባይልካቸዉም ማግኘት ይቻላሉ።
በተመሣሣይ በ Evangelischen Zentrum Höchst የሚገኘዉ የሥነ አዕምሮ ምክር ሰጪ ቢሮ በቅርብ ለተወዱና ለትናንሽ ሕጻናት የምክር አገልግሎት ይሰጣል።
ስለ ልጅዎ እድገትና አስተዳደግ ብዙ ጥያቄዎችን ሕጻኑ ከተወለደ ግዜ ጀምሮ ሦስት ዓመት እስኪሞላዉ ድረስ የምክር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። ከእርስዎ ጋር በጋራ ሆነን ለሚከተሉት ችግሮች መፍትሔ እናፈላልጋለን፣ ለምሣሌ
- በተደጋጋሚ የሚጮህ ከሆነ
- የእንቅልፍ ችግር ካለ
- በምግብ አወሳሰድ ላይ
- የመለያዬት /የወላጆች/ ፍርሃት
- እንቢተኝነት
- ጭንቀት ማስወገድ
- እና ሌሎችም እርስዎን የሚያስጨንቁ ጉዳዮች ካሉ
Ziehenschule ሲሄን ት/ቤት
በትምህርት ጊዜ ለቤቴሰብ፣ ስለ አስተዳደግ ና ለወጣቶች በ Evangelischen Zentrum Am Weißen Stein የምሰጠዉ የምክር አገልግሎት በ Ziehenschule ት/ቤት በአንድ የምክር ክፍል ዉስጥ ሁሌ ማክሰኞ ማክሰኞ ከ 12-14 ሰዓት ይሰጣል።
ይህ የምክር አገልግሎት ከት/ቤት የምክር አሰጣጥ ጋር ጠተጣመረ ሲሆን አስተማሪ ሲሊካቸዉ፣ ባይልካቸዉም የምክር አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል።
አንዳንድ ችግሮችን አንድ ሰዉ ብቻዉን ሊፈታ አይችልም። እንዲህ ሲሆን ደግሞ ምክር ጠቀሜታ አለዉ ይረዳል። እኛንም ለመተዋወቅ ጎራ ብለዉ ይጎብኙን፣ ወይም ደግሞ ከጓደኞችዎ ዉስጥ ችግር የገጠመዉ ካለና ጉዳዩ ካሳሰበዎት። በጋራ መፍትሔ እንፈልጋለን፣ እራስን በራስ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ምክር እንሰጣለን።