በመለያዬትና በፍቺ ግዜ የሚከሰቱ ግጭቶች በስምምነት የመፍታት የምክር አገልግሎት ስለመስጠት

ይህ ግጭቶችን በስምምነት የመፍታት የምክር አገልግሎት ለልጆችዎ ሲባል ሁሉም በጋራ የተስማማበት ዉሎች ላይ ለመድረስ ይረዳዎታል።

የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲገጥምዎት ከእኛ ጋር ግኑኝነት ያድርጉ :

  • ከትዳር ጓደኛዎ ጋር ተለያይተዉ ከልጆች ጋር ያለዉ ግኑኝነትና የአስተዳደግን መብት በተመለከተ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ነዉ?
  • ገለልተኛ ከሆነ ሦስተኛ ወገን ድጋፍ ይፈልጋሉ ?
  • ለልጆችዎ ሁለገብ ደህንነት ሲሉ በጋራ ለመግባባት ይፈልጋሉ ?

አልፎ አልፎ ቤቴሰቦች ተለያይተዉ ወይም ተፋተዉ ሲኖሩ ከልጆች ጋር ያለዉ ግኑኝነትና የአስተዳደግን መብት በተመለከተ ያለ ሦስተኛ ወገን እርዳታ ሊስማሙ አይችሉም። ግጭቶችን በስምምነት የመፍታት የምክር አገልግሎት ቢያገኙ የጠፋዉን የመተማመን ሁኔታ መልሰዉ መገንባት ይችላሉ። በመሆኑም ለልጆችዎ ሲባል ሁሉም በጋራ የተስማማበት ዉሎች ላይ ለመድረስ ይረዳዎታል። የህ ከሆነ ደግሞ አንድ የፍርድ ቤት ዉሳኔ አያስፈልግም።

ሦስት መሠረተ ሐሳቦች የአንድን ምክር አሰጣጥ ይወስናሉ:

  • ሕጻናቶች ከሁለቱም ወላጆቻቸዉ ጋር ጥሩና የጠበቀ ግኑኝነት ይፈልጋሉ
  • ግኑኝነት በፍርድ ቤት ዉሳኔ ሊታዘዝ አይችልም
  • ወላጆች በመለያዬት ግጭት ግዜ አንዱ ወላጅ ልጆቻቸዉ ከሌላዉ ወላጅ ጋር ጥሩ ግኑኝነት እንዲኖር መደገፍ ይችላል

ግጭቶችን በስምምነት የመፍታት የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚመለከተዉ ፍርድ ቤት ማስተላለፍ ይችላል። እርስዎ ይህን የምክር አገልግሎት ለማግኘት ፍ/ቤቱን በማመልከቻ መጠዬቅ ይችላሉ

በፍራንክፌርት ና በኦፍንባህ የካርታስ ጥምርና የኢቫንጌሊካን የክልል ጥምር ከ 2009 ጀምሮ ልክ የፍርድ ቤቱ አሠራር በሚቀርብ መልኩ የምክር አገልግሎት ይሠጣሉ ።

Kontakt zur Terminvereinbarung

Mandy Hanke

Sekretariat

Frankfurt

069 / 53 02 221

E-Mail

Andrea Schare

Sekretariat

Höchst

069 / 75 93 672 10

E-Mail