በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ወደ እኛ ይምጡ ለምሣሌ :
- በልጆችዎ የተነሣ ሁሉም ነገር ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛል የሚል ስሜት ካደረብዎት
- ልጅዎ ከጓደኞቹ፣ በመዋዕለ ሕጻናት፣ በትምህርት ቤት ወይም በሙያ ሥልጠናዉ ላይ ችግሮች ካጋጠሙት
- በልጅ አስተዳደግ ዙሪያ እርግጠኛ ካልሆኑ ወይም ካልተስማማችሁ
- ልጅዎ ወደ ጉርምስና እየመጣ ነዉ፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ ችግር ካለ
- በትዳር ጓደኛዎ ና በቤቴሰብ ሕይወት ዉስጥ ግጭቶች ካሉ
- ከትዳር ጓደኛዎ ጋር ተለያይተዋል ወይም ለመለያዬት ወይም ለመፋታት በሐሳብ ላይ ሆነዉ ሁኔታዎችን እንዴት ኧእንደሚያስከዱት ካላወቁ
- በቅርብ ልጅ አግኝተዉ ሁሉንም ነገር በትክክል ለልጅዎ ማድረግ ከፈለጉ
- እርጉዝ ኖት ብዙ ጣያቄዎች አለዎት
የምክር አገልግሎቱ በፍቃደኝነትና ከክፊያ ነጻ ነዉ። ሁሉም ምክሮችና ውይይቶች ሚስጥርነታቸዉ የተጠበቀ ነዉ። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አስተርጓሚዎችንም እናቀርባለን።
በሙያቸዉ ክህሎት ያላቸዉ አማካሮዎቻችን በትምህርት አሰጣጠጥ ዜዴ፣ በሥነ አእምሮ ና በማህበራዊ ግኑኝነት ዜዴ የተመረቁ ናቸዉ። እኛ ጉዳዩ ከሚመለከተዉ መ/ቤት የጥራት አገልግሎት እንደምንሰጥ ማህተም /das Siegel „Geprüfte Qualität“/ ከፌደራል የአስተዳደግ ምክር ኮንፈረስ /des Fachverbandes „Bundeskonferenz für Erziehungsberatung“/ ተሰጥቶናል።