የኢቫንጌሊካን የክልል ጥምረት ከሁለቱ ማለትም ከኦፍንባህና ከፍራንክፌርት ኢቫንጌሊካን ቤቴክርስቲያናት /Kirchengemeinden und des Evangelischen Stadtdekanates in Frankfurt und Offenbach/ በጋራ የመሠረቱት ነዉ። ወጣቶችን የመርዳትና ማህበራዊ አገልግሎት የመስጠት በሕግ እዉቅና ያለዉ ሲሆን በሁለቱም ከተሞች ለሚኖሩ ሕዝቦች የተለያዩ ማህበራዊና ሥልጠናዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሟት አሉን። በአንደኛዉ ሙያዊ መምሪያ የኢቫንጌሊካን የሥልጠና ተቋሟት፣ የኢቫንጌሊካን ለወጣቶች እርዳታ የሚሰጡ ተቋሟትና የኢቫንጌሊካን የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ተቋሟት በዚህ መምሪያ ሥር ተካተዋል።
እኛ ካለፉት 55 ዓመታት አንስቶ በግለሰብ ደረጃ ችግር ያለባቸዉን ሰዎች፣ አደጋ ላይ የወደቁ፣ ወይም ግጭት ዉስጥ ለገቡት የምክር አገልግሎት እንሰጣለን። ሁሌም ዓላማችን በፍራንክፌርት ያሉትን ሰዎች እራሳቸዉን ችለዉ ሕይወታቸዉን እንዲመሩና ከሕብረተሰቡም ጋር በጋራ የሚኖሩበትን ብቃት ማስጨበጥ ነዉ። እኛ እንደ ኢቫንጌሊካን ቤቴክርስቲያን በፍራንክፌርትና በኦፍንባህ ይህ ጥረታችን ክርስቲያናዊ እምነታችንን መሠረት ያደረገ፣ ሰዉን የመርዳት፣ ተባብሮ አብሮ የመኖር፣ የራስን ሕይወት በራስ የመምራት፣ ሐላፊነትን መቀበልና በሕብረተሰቡ ሕይወት ዉስጥ ተካፋይ እንዲሆኑ መርዳት ነዉ።
እኛ የምንሰጠዉ አገልግሎት በመሠረቱ በከተማችን ነዋሪ ለሆኑት ሁሉ ነዉ። ለምክር አገልግሎት መስጫ ክፍት በሆኑ ተቋሟቶቻችን ለሰዎች የምንሰጠዉ ምክር በነጻ ሲሆን ከዘር፣ ከሃይማኖት፣ ከዬት መጣ ሳይባል፣ በጾታ ወይም በግብረ ሥጋ ግኑኝነት እምነቱ ላይ ምንም ተጽዕኖ ሳይደረግ ነዉ። በሦስቱ ቦታዎች ማለትም በ Eschersheim, Höchst und Offenbach የሚገኙ የምክር መስጫ ተቋሟቶቻችን ለቤቴሰብ፣ ስለ ልጅ አስተዳደግና ለወጣቶች ምክር ይሰጣሉ፣ በተጨማሪም በትዳርና ሕይወት ዙሪያ፣ ማህበራዊ ምክር እንዲሁም በስደትና በፍልሰት ዙሪያ፣ ለስደተኞች ምክርና ሙያዊ ሕክምና፣ ሱስን በተመለከተ ማለትም የአልኮሆልና የጨዋታ ሱስ፣ ስለ ዕዳም ጨምሮ የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ። በአምስቱ ትላልቅ የመኖሪያ ቤቶቻችን ለስደተኞች ማህበራዊ ምክር እንሰጣለን።
በዘጠኙ መሥሪያ ቤቶቻችን ከ 50 በላይ ሠራተኞች እየሰሩ ይገኛሉ። ሁሉም ከዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ሙያዎች ማለትም በሥነ አእምሮ፣ በአስተማሪነት፣ በፖለቲካ፣ ወዘተ የተመረቁ ሲሆን በምክር መስጠት አገልግሎት ዙሪያም ተጨማሪ ትምህርቶችን ያገኙ ስለሆነ ሙያን መሠረት ያደረገ ምክር ከእነሱ ያገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ ሥልጠና የተሰጣችዉ የፍራንክፌርት ከተማ የበጎ ሥራ አድራጊዎችም የምክር ሰጪ ተቋሟቶቻችንን ይረዳሉ፣ ክትትል የማድረግና እራሳቸዉን በራሳቸዉ የሚመሩ ቡድኖችን አመራር በመስጠት ይሠራሉ።
ለተጨማሪ መረጃ