የሚከተሉት ጉዳዮች ሲገጥምዎት ከእኛ ጋር ግኑኝነት ይፍጠሩ:
- ስለ ሰሰኝነት የሚያሳዩ እቃዎችን ያለገደብ ያያሉ /ይጠቀማሉ/ ወይ ?
- እርስዎ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት ፍላጎቴን መቆጣጠር አልችልም ብለዉ ይገምታሉ ?
- ሁሌ በሐሳብዎ የሚመጣዉ ስለ ግብረ ሥጋ ግኑኝነት ነዉ፣ በዚህም የተነሣ ሌላ ሥራዎች መሥራት ይከብድዎታ፤ መሥራት አይችሉም ?
- በሰሰኝነት ተግባርዎ ሲቃይ አለብዎት ?
- የግብረ ሥጋ ግኑኝነት አብሮ ከመኖር፣ ከጓደኝነት ወይም ከሥራ ይበልጥብዎታል ?
በሰሰኝነት ዙሪያ ማንኛዉንም መረጃዎች ከእኛ ያገኛሉ። እኛ በሰሰኝነትዎ ዙሪያ ገለልተኛና ከማንኛዉም ቅድመ ፍረጃ ነጻ የሆነ የምክር አገልግሎት እንሰጥዎታለን።
እኛ እርስዎ ከፈለጉ እርስዎን ለብቻ፣ ከትዳር ጓደኛዎ ጋር ወይም ከቤቴሰብ አባላት ጋር የምክር አገልግሎት እንሰጣለን ።
የሱሰኝነት ሕመምን ለማከም የተለያዩ የሚደማመሩ አርዳታዎች ያስፈልጋሉ። በመሆኑም እኛ ከተለያዩ የሙያ ክሊኒኮች ጋር፣ እራሳቸዉን በራሳቸዉ ለመርጋት ከተቋቋሙት ቡድኖች ጋር፣ እዳ ላለባቸዉ ሰዎች ምክር ከሚሰጡ አማካሪዎች ጋር ና ከሌሎችም ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ መ/ቤቶች ጋር እንሰራለን።
የምክር አገልግሎቱ በፍቃደኝነት ሲሆን ከክፊያ ነጻ ነዉ። ሁሉም የምክር አገልግሎታችን /ንግግሮች/ ሚስጢርነታቸዉ የተጠበቀ ነዉ። አስፈላጊ ከሆነ ለምንሰጥዎት የምክር አገንግሎት አስተርጓሚዎችን እናቀርባለን።
Ihre Ansprechpartner*innen