ያልተፈቀዱ አድንዛዥ ዕጾች

ይህ እርስዎን ወይም ባልደረባዎን የሚመለከት ከሆነ መሠረታዊ ምክር ለማግኘት ወደ እኛ ይምጡ።

እኛ የምንሰጥዎት አገልግሎት፣

  • ሄሮኢን፣ ካኒባስ፣ አምፔታሚኔ ወዘተ በተመለከተ መረጃዎችን መስጠት
  • ገለልተኛና ከእርስዎ ማንነት ጋር ያልተያያዝ የአደንዛዥ ዕጽ ፍጆታዎን ለመገመት
  • ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር ችግር ያለባቸዉን ሰዎች ምክር መስጠት
  • በተመሣሣይ ሁኔታ ችግሩ ካለበት ሰዉ ዙሪያ ያሉ ሰዎችን መምከር

እኛ በግል፣ በጥንድ ወይም በቤቴሰብ ደረጃ የምክር አገልግሎት እንሰጥዎታለን።

የአደንዛዥ ዕጽ ሕመምተኛን ለማከም ወይም ለመርዳት ብዙ ና ሁለን አቀፍ እርዳታ ያስፈልጋል። በመሆኑም እኛ የአድንዝዥ ዕጽ ከሰዉነት ዉስጥ ማስወገጃ ጣቢያዎች፣ ከሙያ ክሊኒኮች፣ ከእራስን በራስ መርዳት ቡድኖች፣ ከእዳ ጉዳይ አማካሪዎች ና ከማህበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር አብረን እንሰራለን።  

እኛ ከ 15 እራስን በራስ መርዳት ቡድኖች ጋር እንሰራለን። እነዚህ  እራስን በራስ መርዳት ቡድኖች የተዋቀሩት  በፍሬንዴክራይስ ፍራንክፌርት (Freundeskreis Frankfurt) ነዉ። የፍሬንዴክራይስ ፍራንክፌርት (Freundeskreis Frankfurt) ለሁሉም የሱስ ችግሮች (አልኮል, ያልተፈቀዱ አደንዛዥ ዕጾች, የዕድል ጨዋታዎች, የጠባይ ችግር) ምክር ይሠጣል። የተጠቂው ግለሰብ ዘመዶችን ወይም የሴቶች ቡድን መሠረት ያደረጉ ሌሎችም የሱሰኞች እራስን በራስ መርዳት ቡድኖች አሉ። እርስዎ በአንዱ እራስን በራስ መርዳት ቡድን ዉስጥ እንዲታቀፉ እኛ እንረዳዎታለን። 

አማካሮዎቻችን ከማህበራዊ ፔዳግጂክ፣ ከማህበራዊ አገልግሎት ሠራተኞ፣ ከሥነ አእምሮ ባለሙያዎች የተዉጣጡ ናቸዉ።

Ihre Ansprechpartner*innen

Monika Schiemann

Sekretariat & Anmeldung

Frankfurt

069 / 53 02 302

E-Mail

Beate Fuchs

Beratung

Höchst

069 / 75 93 672 60

E-Mail

Anzhelina Blum

Beratung & Therapie

Frankfurt

069 / 53 02 303

E-Mail

Katrin Werland

Beratung & Therapie

Frankfurt

069 / 53 02 305

E-Mail