እርስዎ በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ከእኛ ጋር ግኑኝነት / ኮንታክት/ ያድርጉ፣
- ዘመድዎ ወም ጓደኛዎ ሱሰኛ ነዉ ?
- አጠቃላይ ሕይወትዎ አቅጣጫዋን የሳተች ይመስልዎታል ?
- ለመርዳት ማድረግ የሚገባዎትን ሁሉ አድርገዋል ? እርስዎ መክረዋል፣ ረግመዋል፣ አስፈራርተዋል፣ ጮሄዉበታል ና ሌላም አድርገዋል ?
- አደርጋለሁ ብሎ ቃል የሚገባዉን ሁሉ በተደጋጋሚ መልሶ ያደርጋል ብለዉ ያምናሉ ?
- „ጥፋት አድርጌአለሁ ብለዉ“ እራስዎን ይወቅሳሉ ?
- ጓደኛዎ ወይም ልጅዎ ሱሰኛ ለመሆኑ የእኔ ጥፋት ነዉ ይላሉ ?
- እርስዎ በሃሳብዎ በተስፋና እምነትን ወይም የተገባዉን ቃል ደጋግሞ በማጉደል መካከል ላይ ነዉ ይላሉ ?
- እርስዎ በሕይወት ለመቆዬት ፍራቻ፣ ንዴት፣ ተስፋ መቁረጥ ና ምንም ማድረግ የማይችሉ ዓይነት ስሜት አለዎት ወይ ?
- እርስዎ አልፎ አልፎ የአቅም አልባነት ስሜት አለዎት ?
- እርስዎ ሕይወትዎን ሙሉ ለችግሩ ተጠቂ አድርገዉ አሳልፈዉ ሰጥተዋል ወይ ?
ሱሰኝነት የእለት ተእለት ሕይወትዎን ከወሰነ፣ ይህ ደግሞ ወደ ከፍተኛ የገንዘብ ና ማህበራዊ ችግሮችን ወይም ቀዉሶችን ወስጥ ያስከትላል። በዚህም የተነሣ በዙሪያዎም ያሉት ሁሉ ከእርስዎ ጋር ያዝናሉ፣ ዉሸቶች፣ ዋልጌነት ወይም እዳዎች ባልደረባዎን፣ ቤቴሰብዎን ወይም ጓደኞችዎን ወደ ከባድ የአካል ና የገንዘብ ችግር ዉስጥ ይከታቸዋል። እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲገጥምዎት፣ በቅድሚያ ለራስዎ ጥሩ ጥበቃ ማድረግ አለብዎት።
እኛ እርስዎን እንደ ባልደረባነትዎ (ወይም በችግሩ ተጠቂ ከሆነዉ ጋር በማህበራዊ ሕይወቱ ዙሪያ ችግሩ የደረሰባቸዉ ካሉ) በግል ና ወይም በተናጠል የምክር አገንግሎት እንሰጥዎታለን።
እኛ ለተጠቂ ባልደረባዎች ወይም ለተጠቂ ዘመዶችዎ ወርክሾፕ ወይም ሴሚናሮች እንሰጣለን። በስድስት ሣምንታት ልዩነት ለተጠቂ ባልደረባዎች ሴሚናሮች ይሰጣሉ። የተካፋዮች ብዛት በስድስት ና አሥር መካከል ነዉ። ወርክሾፑ ወይም ሴምናሩ የሚመራዉ በቂ ልምድ ባላቸዉ ሁለት አማካሪዎች ነዉ።
Für aktuelle Termine bzgl. des Angehörigenworkshops wenden Sie sich an:
![](https://evangelische-beratung.com/wp-content/uploads/2019/08/Monika-Schiemann_Verwaltung-Suchtberatung-300x200.jpg)
![](https://evangelische-beratung.com/wp-content/uploads/2020/01/portrait_platzhalter-1-300x300.jpg)
![](https://evangelische-beratung.com/wp-content/uploads/2019/08/beate-fuchs_suchtberatung-hoechst-e1576424435131-300x268.jpg)
![](https://evangelische-beratung.com/wp-content/uploads/2019/08/Martin-Meding_Suchtberatung-300x200.jpg)
![](https://evangelische-beratung.com/wp-content/uploads/2020/01/Ralf-Hoelzel_Suchtberatung-300x300.jpg)