እኛ በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ድጋፍ እንሰጥዎታለ፣
- እርስዎ ከተፋቱ በኋላ /ልጆቸን/ የማሳደግ ና የማዬት መብትን በተመለከተ በፍርድ ቤት በመከራከር ላይ ኖት ?
- እርስዎ ለምክር ገለልተኛ ና ሦስተኛ ሰዉ ይፈልጋሉ ?
- እርስዎ ለልጅዎ ጤናማ እድገት ሲሉ በጋራ / ከባሌቤትዎ ጋር / ተነጋግረዉ መፍትሔ ለማግኘት ይፈልጋሉ ?
ግጭቶችን በምንፈታበት ምክሮቻችን የተከሰተዉን የእምነት ማጣት በማስወገድ የጋራ መተማመንን እንደገና እንገነባለን። በዚህ መልኩ ለልጆችዎ ጤናማ እድገት ሲትሉ በጋራ የምትግባቡት ስምምነቶችን ማመቻቸት ይቻላል።
ሦስቱ መሠረታዊ መርሆች፣
ሕጻናታ ከሁለቱም ወላቾች ጋር ጥሩ ና ጠንካራ ግኑኝነት ይፈልጋሉ
ግኑኝነቶች /ጤናማ / በፍርድ ቤት ዉሳኔ ወይም በትዕዛዝ ሊመጡ አይችሉም
ወላጆች በመለያዬት ጊዜ ግጭት ቢኖርም አንዱ ወላጅ ልጆች ከሌላው ወላጅ ጋር ያላቸዉን ግኑኝነት ጥሩ እንዲሆን መርዳት ይችላል።
ግጭቶች በድርድር እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሚሰጠዉ ጉዳዩ የሚመለከተዉ ፍርድ ቤት ነዉ። እርስዎ ፍ/ቤቱን ለዚህ ጉዳይ በማመልከቻ መጠዬቅ ይፍላሉ።
እ.አ.አ. ከ 2009 ጀምሮ በፍራንክፌርት ከተማ /Frankfurt/ የካርታስ ማህበር (Caritasverband) ና የፍራንክፌርቱ ክልላዊ አኢቫንጌሊካን ሕብረት (Evangelische Regionalverband Frankfurt) ይህን ከፍርድ ቤት ሂደት ጋር የተቀራረበ ምክር ይሠጣሉ።
Kontakt zur Terminvereinbarung