በሚከተሉት ርዕሶች ዙሪያ ወደ እኛ ይምጡ:
- እርስዎ የሥነ አዕምሮአዊ ምክር ና ሕክምና ይፈልጋሉ ?
- ፍርሃቶች አሉብዎት ወይም ያዝናሉ ?
- ነገሮችን ማስታወስ አይችሉም፣ ይረሳሉ ?
- ሌሊት መተኛት አይችሉም ?
- በድንገት ይነቃሉ ልብዎ በጣም ይመታል ?
ስደት፣ ድብደባ ና ሌሎች በሃይል የተደገፈ በደል በ አዋቂዎች፣ በወጣቶች ና ሕጻናት ላይ ጠባሳን ትተዉ ያልፋሉ። የምክር አገልግሎታችንን ይጠቀሙ። እኛ ሥነ ልቦናዊና አካላዊ ቁስልዎን እንዲሁም የደረስብዎት መጥፎ በደሎች በመጠኑ ለመቀነስ አብረንዎት በመሥራት እንረዳዎታለን።
አማካሪዎቻችን የሥነ ልቦና ምርመራ፣ ምክር ና ሕክምና በጀርመንኛ ቋንቋ በአስተርጓሚዎችም በመረዳት ሙያዊ ምክር ይሰጣሉ።
ሚስጢነቱ የተጠበቀ ምክራችን በፍቃደኝነት ሲሆን ከክፊያ ነጻ ነዉ።
Kontakt zur Terminvereinbarung